=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ብልህና አስተዋይ የሆነ ሰው ኪሳራን ወደ ትርፍ ይለውጣል። መሀይም እና ቂል የሆነ ሰው ግን አንድን መከራ ሁለት ያደርገዋል። መልእክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) ከመካ ሲባረሩ መዲና ውስጥ ዝናው የታሪክን መስሚያና ማያ ያጣበበ ሀገር መሠረቱ። ኢማሙ አህመድ ሐምበል ታስሮ ቢገረፍ መጨረሻ ላይ የሱና መሪ ሆነ። ኢብኑ ተይሚያ ቢታሰር ከእስሩ እጅግ ብዙ እውቀት ይዞ ወጣ። ሠርኸዚ ውሃው የደረቀ ጉድጓድ ውስጥ ቢያስቀምጡት በፊቅህ ዙሪያ 20 ጥራዞችን ፃፈ። ኢብኑል አሲር በበሽታ ምክኒያት ቢቀመጡ ጃሚዐል ኡሱል እና አሕያን ደረሰ እነሱም በጣም ጠቃሚ ከሆኑ የሐዲስ መፅሐፎች ውስጥ ይቆጠራል። ኢብኑል ጀውዚ ከባግዳድ ሲባረሩ 7ቱን አቀራሮች አሳምረው ተማሯቸው። ማሊክ ኢብኑ ረይብን ጣዕረሞት ሲደርስበት የአባሲያ ግዛት ገጣሚዎች የግጥም መድብሎችን የምታስንቅ ድንቅ የግጥም መድብል ፃፈ። የኢቢዙአይብ አል-ሁዘሊይ ልጆች ሲሞቱ ዘመን ያዳመጣት አድማጭ የተገረመባት ተራኪውም ያጨበጨበላትን ምርጥ የሀዘን ግጥም ፃፈ።
አንድ ችግር ሲያጋጥምህ ብሩህና መልካም ጎኑን ለመመልከት ሞክር። አንድ ሰው የሎሚ ጭማቂ በብርጭቆ ቢሰጥህ ትንሽ ስኴር ጨምርበት። ዘንዶ በስጦታ መልክ ቢሰጥህ ውዱ ቆዳውን ወስደህ የተቀረውን ተወው። ጊንጥ ቢነድፍህ ደግሞ የእባብ መርዝ ፍቱን መከላከያ ክትባት መሆኑን እወቅ።
ከአስቸጋሪ ግዜያቶች ጋር ለመጣጣም ሞክር ፤ አበባ እና ፅጌሬዳም አትርፍባቸው። እንዳችን ነገር ልትጠሉ አሏህም በርሱ ብዙ ደግ ነገርን ሊያደርግ ይችላል።
ፈረንሳይ ከአብዮቱ በፊት ሁለት በገድ የሚያምንና መልካም ነገሮችን የሚመኝ ገጣሚዎችን አሰረች። ሁለቱም በእስር ቤቱ መስኮት ጭንቅላታቸውን ቢያወጡ ሁለተኛው ወደ ኮከቦች ተመልከቶ ሲስቅ አንደኛው ደግሞ በአቅራቢያው ባለው መንገድ ላይ ጭቃ አይቶ አለቀሰ። ሁሌም የመከራን ሌላኛውን ብሩህ ገፅታ የማየት ልምድ ይኑርህ። ምክኒያቱም ሙሉ በሙሉ ሁሉም ገፅታዎቹ ክፉ የሆኑ ምንም ነገር የለም ፤ ባይሆን በውስጣቸው መልካም ነገሮች ትርፎች እና ምንዳም አላቸው።
<•> አስብና ተነስ የለዉጥ ቁልፍ በእጅህ ነዉ።
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|